አማርኛ ስድስተኛ ክፍል 11 Sections47 Lessons365 Days
1.2. ንባብ
ባህላዊ አለባበስ
የ6ኛ ክፍል አማርኛ ትምህርት
የትምህርቱ አላማዎች
ተማሪዎች ይህንን ትምህርት ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡-
በምንባቡ ውስጥ ላሉ አዳዲስ ቃላት (እንደ ቱሪስት፣ ሀሴት፣ ሁለንተናዊ) አውዳዊ ፍቺ ትሰጣላችሁ፡፡
ስለ ኢትዮጵያ ባህላዊ አለባበሶች የቀረበውን ምንባብ ዋና እና ዝርዝር ሀሳቦች ትለያላችሁ፡፡
ቃላትን በመነጠል እና በማጣመር አቀላጥፋችሁ ታነባላችሁ፡፡
ባህላዊ አልባሳት ለማንነታችን እና ለባህላችን ያላቸውን ጠቀሜታ ትገልፃላችሁ፡፡
አዳዲስ ቃላትና ፍቺያቸው
ቱሪስት
ከአንድ ሀገር ወደ ሌላ ሀገር አዳዲስ ነገሮችን ለማየትና ለመጎብኘት የሚሄድ ሰው (ጎብኚ)፡፡
ሀሴት
ከፍተኛ የሆነ የደስታ ስሜት፣ ፍስሀ፣ እርካታ፡፡
ሁለንተናዊ
አጠቃላይ የሆነ፣ ሁሉንም ነገሮች ያካተተ፣ ሙሉ በሙሉ፡፡
ባህላዊ መገለጫ
የአንድን ማህበረሰብ ማንነት፣ እሴትና ልማድ የሚያሳይ ምልክት ወይም መታወቂያ፡፡
ያልተበረዘ
ከሌላ ባዕድ ነገር ጋር ያልተቀላቀለ፣ ንፁህ፣ ያልተከለሰ ኦሪጅናል ባህል፡፡
አሞሌ
በጥንት ዘመን በኢትዮጵያ እንደ ገንዘብ ያገለግል የነበረ የጨው ቅርፅ፡፡
ቅድመ ንባብ ተግባራት
ተግባር አንድ፡ የምስል ምልከታ
ተማሪዎች የሚከተሉትን ጥያቄዎች በቃል መልሱ፡-
- በርዕሱና በምስሉ መካከል ያለውን ዝምድና ግለጹ፡፡
- ርዕሱን ተመልክታችሁ ምንባቡ ስለ ምን የሚናገር ይመስላችኋል?
ተግባር ሁለት፡ ቃላትን መነጠልና ማጣመር
ምንባቡን ከማንበባችሁ በፊት የሚከተሉትን ቃላት በመነጠልና በማጣመር አንብቡ፡፡
| ተ.ቁ | ነጥሎ ማንበብ | አጣምሮ ማንበብ |
|---|---|---|
| 1 | በየ – አለባበስ -ኦች – ኣችን | በየአለባበሶቻችን |
| 2 | የ – ሁለንተ – ናዊ | የሁለንተናዊ |
| 3 | ከ – አስ- ተዳደግ – ኣችን | ከአስተዳደጋችን |
| 4 | የ – ሚመረት – ኡ – በት -ና | የሚመረቱበትና |
| 5 | ተወዳጅ – ነት – ኣቸው | ተወዳጅነታቸው |
| 6 | የ – ተዥጎ – ረጎረ | የተዥጎረጎረ |
| 7 | ባህል – ነት -ኣቸው – ን | ባህልነታቸውን |
የንባብ ሂደት (Reading Comprehension)
የሚከተለውን ምንባብ በለሆሳስ አንብቡ፡፡ ስታነቡ ግልፅ ያልሆነ ሀሳብ ሲያጋጥማችሁ በማስታወሻ ፃፉ፡፡
ባህላዊ አለባበስ
ኢትዮጵያዊያን እንደየ ባህላችን በልዩ ልዩ ቅርፅና ቀለማት ያሸበረቁ ባህላዊ አለባበሶች አሉን፡፡ እነዚህ ባህላዊ አለባበሶቻችን የሁላችንም የሁለንተናዊ ማንነታችን መገለጫዎች ናቸው፡፡ ይህ ውብ የሆነ ያልተበረዘና ያልተከለሰ ባህላዊ አለባበሳችን ሀገራችንን ከሌሎች የአለም ሀገራት እንድትለይ ያደርጋታል፡፡ ባህላዊ አለባበሳችን ከማንነታችን የሚመነጭ ሲሆን ከተለያዩ ሀገራት በሚመጡና እኛም ወደ ተለያዩ ሀገራት ስንሄድ በአሸበረቀው ባህላዊ አለባበሳችን ውበት የሚደነቁት ብዙዎች ናቸው፡፡
ከሌሎች ሀገራት አለባበሶች የኛን ልዩ የሚያደርገው የራሳችንን የፈጠራ ስራ የሚያካትት መሆኑ ነው፡፡ በተለያዩ የደስታና የሀዘን ስሜቶች የምንላበሳቸው ባህላዊ አለባበሶቻችን ለስራው የሚሆኑትን ጥሬ እቃዎች፣ የሚመረቱበትና ወደልብስነት የሚለወጡት በራሳችን ጥበብ ነው፡፡ እንደየባህላችን በተለያዩ ጥልፎች፣ጌጣጌጦችና ጥበቦች ያሸበረቁ ባህላዊ ልብሶችን ለብሰን ልዩ ልዩ ባህላዊ ክንውኖችን ስንከውን ልዩ ህብር ፈጥሮ ስሜትን ይቀሰቅሳል፡፡
ባህላዊ አለባበሶቻችን ከጊዜ ወደ ጊዜ አለምአቀፋዊ ተወዳጅነታቸው እየጨመረ መጥቷል፡፡ የተወዳጅነት ሚስጥሩም ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት ጎብኝዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየጨመረ መምጣቱ ነው፡፡ በአለባበሳችን ተማርከው እነሱም የተለያዩ አልባሳትን እየገዙ በመልበስ ሀሴትን መጎናፀፍ ችለዋል፡፡ እነዚህም ባህላዊ አለባበሶች በተለያዬ አመታዊ ክብረ በዓላትና ህዝባዊ በአላት ማለትም በሰርግ፣ በጥምቅት፣ በአረፋና በመውሊድ መሰል አጋጣሚዎች ይለበሳሉ፡፡
እነዚህ ባህላዊ አለባበሶች እንደየ ህብረተሰቡ ባህል በተለያዩ ቀለማት የተዥጎረጎሩ ሆነው በቀሚስ፣በነጠላ፣ በኮትና በሱሪ መልክ ልንለብሳቸው እንችላለን፡፡ የወንድና የሴት፣የወጣቶችና የአዛውንቶች፣ እንደየ እድሜ ደረጃችን የባህሉ አሻራ ያረፈባቸውም ናቸው፡፡ በዚህ መካከል በየአለባበሳችን የባህል ልውውጥ መኖሩን የሚያሳዩ ሲሆን የማንነታችን መገለጫዎች ከመሆናቸው ባሻገርም አምረንና ተውበን እንድንታይ ያስችላሉ፡፡
ባህላዊ አለባበሳችን ለቀጣዩ ትውልድ የምናወርሳቸው ውድ ቅርሶቻችን ናቸው፡፡ ‹‹ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለውም›› እንደሚባለው ባህላዊ አለባበሶቻችንን ለተተኪው ትውልድ ለማስተዋወቅና ለማስተላለፍ እንዲሁም ባህልነታቸውን ጠብቀው እንዲቆዩ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል፡፡
ምንጭ፡ ፈንታሁን እንግዳ (2000) ታሪካዊ መዝገበ ሰብዕ
አንብቦ መረዳት (እውነት ወይም ሀሰት)
ቀጥሎ የቀረቡትን ጥያቄዎች ካነበባችሁ በኋላ ትክክል ከሆኑ ‹‹እውነት›› ትክክል ካልሆኑ ‹‹ሐሰት›› በማለት መልሱ፡፡
የቃላት ልምምድ
በምንባቡ ውስጥ ላገኟቸው አዳዲስ ቃላት የተሰጠውን ፍቺ መሰረት በማድረግ ትክክለኛውን መልስ ምረጡ ወይም ፃፉ፡፡
የማጠቃለያ ነጥቦች
ባህላዊ አለባበሶች የሁለንተናዊ ማንነታችን መገለጫዎች እና የሀገራችን መለያዎች ናቸው፡፡
የኛ ሀገር አልባሳት ከሌሎች የሚለዩት የራሳችን የፈጠራ ስራና ጥበብ የሚታይባቸው በመሆኑ ነው፡፡
ባህላዊ አልባሳት በአለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው ተወዳጅነት እያደገ መጥቷል፡፡
ባህላችንን ጠብቀን ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የሁላችንም ኃላፊነት ነው፡፡
ተግባር ሶስት፡ የንባብ ፍጥነትና መረዳት
ተማሪዎች ከዚህ በታች የቀረበውን አንቀፅ በጥንድ በመሆን ደቂቃ እየያዛችሁ በተገቢው ፍጥነት አንብቡ። በመቀጠልም ጥያቄዎቹን መልሱ፡፡
ለፍጥነት ንባብ የቀረበ
ባህላዊ አለባበሶቻችን ከጊዜ ወደ ጊዜ አለማቀፋዊ ተወዳጅነታቸው እየጨመረ መጥቷል፡፡ የተወዳጅነት ሚስጥሩም ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት ጎብኝዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየጨመረ መምጣቱ ነው፡፡ በአለባበሳችን ተማርከው እነሱም የተለያዩ አልባሳትን እየገዙ በመልበስ ሀሴትን መጎናፀፍ ችለዋል፡፡ እነዚህም ባህላዊ አለባበሶች በተለያዩ አመታዊ ክብረ በዓላትና ህዝባዊ በአላት፣ በሰርግ፣ በጥምቀት፣ በአረፋና በመውሊድ መሰል አጋጣሚዎች ይለበሳሉ፡፡
የትምህርቱ ማረጋገጫ (Checklist)
በትምህርቱ ያገኛችሁትን ክህሎት አረጋግጡ (Check off)፡